LatestNews

ምክር ቤቱ በቀጣይ 10 ዓመት ተግባራዊ እንዲሆን የተዘጋጀውን የልማት ፍኖተ ካርታ አፀደቀ

በቀጣይ 10 ዓመት በአገር ደረጃ ተግባር ላይ እንዲውል የተዘጋጀውን የልማት ፍኖተ ካርታ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዓመት 11ኛው መደበኛ ስብሰባ አጽድቆታል፡፡የጸደቀው የልማት ፍኖተ ካርታ ተቋማትን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ እና በርካታ ባለድርሻዎች የተሳተፉበት እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡“የ10 ዓመት የመለወጥ፣ የማደግ እና የመሻሻል እቅዳችን ያለፉት 3 ዓመታት የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ዝግጅት እና አፈፃፃምን መነሻ ያደረገ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በምክር ቤት ፊት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ።“በአንድ ልብ ተደማምጠን ከሰራን ኢትዮጵያን በ10 ዓመት የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌነት ለማድረግ ያለመ እቅድ ሲሆን በ30 ዓመት ውስጥ አገሪቱን የዓለም የብልጽግና ተምሳሌነት ማድረግ ያለመ እቅድ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።