LatestNewsSports

ይህን ያውቁ ኖሯል??

በኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ለሀገሩ ያስገኘው ጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ ሲሆን በ 1960 የሮም ኦሎምፒክ በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ ነበር ፡፡

በኦሎምፒክ እጅግ ውጤታማው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሲሆን በውድድሩ ም ታሪክ ለሀገሩ ሶስት የወርቅ እና አንድ የብር ሜዳሊያዎችን አስገኝቶዋል ፡፡

በውድድሩ ታሪክ ብዙ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ደግሞ ጥሩነሽ ዲባባን የሚያክል የለም። ጥሩነሽ በኦሎምፒክ ለሀገሯ ሶስት የወርቅ እና ሶስት የነሃስ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈች ድንቅ አትሌት ነች ።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ የኦሎምፒክ የአትሌቲክስ ስፖርት ውጤታማነት ደረጃ ባስመዘገበቻቸው 54 ሜዳሊያዎች አማካኝነት ከአለም 10ኛ ከ አፍሪካ ደግሞ 2ተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡

ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የሜልቦርን ኦሎምፒክ ውጭ በተሳተፈችባቸው ሁሉም የውድድሩ ተሳትፎዎቿ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች ።

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ ብታደርግም ሁሉንም ሜዳሊያዎች ያገኘችው ግን በአትሌቲክሱ ዘርፍ ነው ፡፡