EthiopiaLatestNews

“የእህቴ ጠባቂ ነኝ”

“የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መልዕክት በአገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው ንቅናቄ አካል የሆነ ህዝባዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ነው ። “ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም”በሚል መሪቃል ነው ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው ሰልፍ ፤ በዚሁ ሰልፍ ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች እንደሚዘጉ የተገለፁ ሲሆን ፤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ማለትም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑትን መንገዶች የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል:: ** በዚህም መሰረት• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ እና ታች መንገዶች • ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ላይ እና ታች መንገዶች• ከ4 ኪሎ በውጪ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ- ቤተ መንግስት• ከአዋሬ ካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ መብራት• ከሜክሲኮ፣ለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር ትራፊክ መብራት ላይ• ከሰንጋ ተራ ብሄራዊ ቴአትር ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት • በቸርችል ጎዳና ፖስታ ቤት፣ ሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ መብራት• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እና ለቀላል ተሸከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ዝግ የሚሆን ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ እና በእነዚህ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለይም ወቅታዊውን የሀገራችንን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ሰላም ወዳድ የከተማችን ነዋሪዎች እንደሁልጊዜውም የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።

Telegram: https://t.me/ebstvworldwide

Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision

#ኢቢኤስ#EBS

90902 Comments3 SharesLikeCommentShare