News

አዲስ ነገር – የሰብዓዊ ድጋፍ ለትግራይ

በትግራይ ለ800ሺህ ዜጎች የሚሆን የምግብ ድጋፍ የጫኑ 308 መኪናዎች ወደመቀሌ መድረሳቸውን የአለም የምግብ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል፡፡
ይህን ድጋፍ ያደረገው የአለም የምግብ ፕሮግራም በአፋርና በአማራ ክልልም በ6 ዙሮች መሰረታዊ የሆነ የምግብ ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር ነው የገለፀው፡፡
በተያያዘ መረጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመረጃ ምንጭ የሆነው ሪሊፍ ዌብ በበኩሉ መጋቢት 23 እስከ ግንቦት 29 ባሉት ቀናት በ18 የጭነት መኪናዎች 65 ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሰሜን ሸዋ እና በዋግኸምራ ዞኖች ለሚገኙ 4 ሺህ 448 ተፈናቃይ ወገኖች የመጠለያና የምግብ ድጋፍ መድረሱ የተነገረ ሲሆን ከደቡብና ሰሜን ወሎ ዞኖች እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞኖች ተፈናቅለው በደብረብርሃን የነበሩ 243 ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉም ተነግሯል፡፡
በሌላ በኩል በአፋር ክልል ደግሞ የምግብ እጥረት የሚስተዋልባቸው ህፃናት ቁጥር ከባለፈው አመት የሚያዚያ ወር ጋር ሲነፃፀር በ28 ከመቶ ስለመጨመሩ ተነግሯል፡፡
መረጃዎቹ የአለም የምግብ ድርጅትና የሪሊፍ ዌብ ናቸው፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New