News

አዲስ ነገር – የፓርላማው ዉሎ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም በፓርላማ ተገኝተው በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተነሱላቸ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በዛሬው የእንደራሴዎች ምክርቤት ውሎ ከአባላቱ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱላቸው ሲሆን በተለይም የምጣኔ-ሀብት፣ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ የጥያቄዎቹን አንኳር ድርሻ ሲይዙ እርሳቸውም በሀገሪቷ እየታዩ ናችው ያሏቸውን ለውጦች ከሶስት አመት በፊት ከነበረው ጋር በማነጻጸር መልሰዋል፡፡
እንዲሁም በምላሻቸው፤ ካልተጠበቁት ተፈጥሯዊ አደጋዎች ማለትም ከጎርፍ፣ ከኮቪድ እና ከመሳሰሉት በተጨማሪ፤ ሰው-ሠራሽ ችግሮች ለሀገራችን ፈተና ሆነው መቆየታቸው የገለጹ ሲሆን ይህም ቢሆን እንኳ ኢትዮጵያ በእነዚህ ምክንያቶች አልፈረሰችም፤ የብልጽግና መሠረቷንም አስፍታለች ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ስለተሰሩና ማስፋፊያ ስለተደረገላቸው መንገዶች፣ ስለ ቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽነት፣ ስለተገነቡ የስኳር ፕሮጀክቶች አንስተው ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በቁጥር ደረጃ ሲያብራሩ ደግሞ ከሶስት አመታት በፊት 4 ያህል የስኳር ፋብሪካዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ 9 መድረሳቸውን እንዲሁም 3 የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደነበሩና አሁን ላይ 15 እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርናው ዘርፍም በዚህ አመት 5 ሺህ ያህል ትራክተሮች ወደ ሀገር ውስጥ እንደገቡ ገልጸው ይህም 28 በመቶ የሚሆነው የእርሻ መሬት በትራክተር እንድናርስ ያደረገናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New