News

አዲስ ነገር – የነዳጅ ድጎማ ስርዓት

የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት በታቀደለት የጊዜ ማዕቀፍ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተነገረ፡፡
ይህ የተባለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለትራንስፖርት ዘርፍ የክልልና ከተማ መስተዳደር ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በብሔራዊ ደረጃ ስለሚተገበረው የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ገለፃና ማብራሪያ በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡
የነዳጅ ድጎማው ከህብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የተቆራኘ መሆኑን ከግምት በማስገባት ጥናት ተደርጎ ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሸከርካሪዎች ተግባራዊ ይደረጋል የሚለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሂደቱም እስካሁን ከነበረው ጥቅል የድጎማ ስርዓት በመውጣት በታቀደለት የጊዜ ማዕቀፍ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡
በእስካሁኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቂ መግባባት ላይ መደረሱን ያስታወቀው ተቋሙ በአዲስ አበባ በፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎትና የከተማ ታክሲ አገልግሎት በሚሰጡ ተሽከርካዎች ላይ ተግባራዊ የተደረገውና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ የለማው የብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ማስተግበሪያ ስኬታማ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New