News

አዲስ ነገር – የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደንበኞቹ በሚሰጠው አገልግሎት ከአፍሪካ ምርጡ ተብሎ በ2022 የአፕኤክ አየር መንገድ ሽልማት ተመርጧል።
ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ጥምረት አካል የሆነውና ለትርፍ ያልተቋቋመው አፔክስ በአየር መንገድ ዘርፍ የደንበኞችን ፍላጎትን ለማርካትና የአየር መገዶችን አቅም ለማጎበት በሚያዘጋጀው ሽልማት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤስት ኢንተርቴንመንት በተሰኘ ዘርፍና በሚሰጠው የግል በረራ መስተንግዶ ነው ከአፍሪካ ቀዳሚው ተብሎ የተመረጠው።
ተሳፋሪዎች ምርጥ የሚሏቸውን አየር መንገዶች ለምርጫ የሚያቀርቡበትና ይገባዋል ያሉትን ደረጃ ይሰጡበታል የተባለው ሽልማቱ በአየርላንድ ደብሊን ከተማ የተካሄደ ሲሆን በዘንድሮው ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ በረራዎችና ከ600 በላይ አየር መንገዶች የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ መመዘኛን በመጠቀም በአለም ዙሪያ በተጓዙ መንገደኞች የተሰጠ ደረጃ ስለመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New