News

አዲስ ነገር – ሱዳን ያነሳችው የድንበር ውዝግብ

የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ።
አቶ ደመቀ መኮንን ይህንን የተናገሩት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ሲሆን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ በተለይም በኢትዮ ሱዳን ድንበር ሰሞናዊ ሁኔታ፣ እየተካሄደ ባለው የሰላም ግንባታ ሂደት፣ ብሄራዊ ምክክር እንዲሁም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ ገለጻ ማድረጋቸው ተገልጿል።
በዚህ ወቅት መንግስት ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ደመቀ ሱዳንም ውጥረት ከማባባስ እንድትቆጠብና ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ለማላበስ የምታደርገውን ሂደት እንድታቆም የጠየቁ ሲሆን ሀገራቱ ከድንበር ጋር በተያያዘ ያለውን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱባቸው በርካታ መንገዶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም እንዲረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝና በትግራይ ክልል ሰብአዊ ዕርዳታ እና አቅርቦት እንዲዳረስ መሥራቱ ገልጽው ከፍተኛ የፖለቲካ ባለሥልጣኖች ከእስር ቤት መለቀቃቸው መንግስት ከህወሓት ጋር ያለውን ግጭት በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ህወሓት ላይ ጫና በማሳደር ከግጭት ቀስቃሽነት ተግባሩ እና ወደ ሌላ ጦርነት ውስጥ ከሚከት ድርጊቱ የሚታቀብበት ሁኔታን እንዲያመቻች የጠየቁም ሲሆን የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ በገባችበት ጊዜ ሁሉ ላሳዩት አጋርነት ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New