News

አዲስ ነገር – ኢትዮጵያና የዝንጀሮ ፈንጣጣ

የጤና ሚኒስቴር በሀገራችን ሁለት ግለሰቦች በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ተይዘዋል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ሲል አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሀገራት እየተከሰተ የሚገኘውና ተላላፊ የሆነው ይህ በሽታ በርካቶችን እያጠቃ የሚገኝ መሆኑን ገልጾ ነገር ግን እስካሁን በኢትዮጵያ በበሽታው ስለመያዙ ሪፖርት የተደረገ ሰው የለም፤ ሁለት ሰዎች ተይዘው በህክምና ላይ ናቸው በሚል እየተነገሩ ያሉ መረጃዎችም ሀሰት ናቸው ብሏል፡፡
የጤና ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ መገናኛ ብዙሀን ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከመዘገብ በመቆጠብ በሀላፊነት እንዲሰሩ ጠይቆ የጤና ስጋት የሚሆኑ በሽታዎችን በተመለከተ ከራሱ ከሚኒስቴሩ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ አልያም ከህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የሚወጡ መረጃዎችን መከታተት እንደሚቻል አመልክቷል።
በነገራችን ላይ ተመልካቾቻችን ይህ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ አሁን ላይ በአፍሪካ በቤኒን፣ካሜሮን፣ ጋቦንና ጋንን በመሳሰሉ ሀገራት የተከሰተት ሲሆን እነዚህን ጨምሮ በመላው ዓለም በሽታው በተከሰተባቸው አገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመያዛቸው ውጪ በበሽታው የተነሳ ህይወቱ ያለፈ ሰው ሪፖርት አለመደረጉን የአለም ጤና ድርጅት መረጃን የጠቀሰው የሪሊፍ ዌብ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New