News

አዲስ ነገር – የታለመለት የነዳጅ ድጎማ

የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ፕሮግራምን በተያዘለት ጊዜ ለማስጀመር የሚያስችሉ ተግባሮች መከናወናቸዉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ቅድመ ዝግጅቶችን በተመለከተ የአስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባን በማካሄድ በመድረኩ የባለድርሻ አካላትን ዝግጅት ገምግመናል ያሉት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ በድጎማዉ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን መረጃ ማደራጀት እንደተቻለም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከሃምሌ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ በመላዉ የሀገራችን ክፍል ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ፕሮግራሙ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ስለመዘጋጀቱ የተጠቆመ ሲሆን የክፍያ ስርዓቱም ሙሉ በሙሉ በቴሌ ብር እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
ብሄራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማን ተግባራዊ ለማድረግ በትራንፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና በኢትዮ ቴሌኮም የለማውን መተግበሪያ በአዲስ አበባ፣ በሃዋሳ፣ ባህርዳር፣ አዳማና ወላይታ ሶዶ ከተሞች የሙከራ ስራዎች ስለመሰራታቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New