Others

አዲስ ነገር – ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ

በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ማንነትን መሰረት ያደረገ የዜጎች ግድያ በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡
ኮሚሽኑ ትናንት ሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ/ም በቄለም ወለጋ ዞን፥ ሃዋ ገላን ወረዳ በዘውግ ማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ግድያ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ደርሰውኛል ያለው ኢሰመኮ የተገደሉ ሰዎች ቁጥርንና ስለ ግድያው ሁነት የማጣራት ሥራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ትናንት ጠዋት በኦነግ ሸኔ አባላት ግድያው እንደተፈጸመ እማኞቼ ነግረውኛል የሚለው ኢሰመኮ በአካባቢው በንጹሃን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ያለ ሲሆን በአካባቢው የተሰማሩ የመንግስት የጸጥታ አካላት ግድያውን ማስቆም በሚያስችል መልኩ እንዲጠናከሩ አሳስቧል፡፡
በተመሳሳይ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በወለጋ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ መንግስት ማንነትን መሰረት አድርገው የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ያሳሰበ ሲሆን ዜጎችን ከአሰቃቂ ግድያ የመጠበቅ መንግስታዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት በተለይም በወለጋ አካባቢ በዚህ ደረጃ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ለምን መቆጣጠር እንደተሳነው ለሕዝብ በግልጽ የማሣወቅ ግዴታ ያለበት ከመሆኑም በተጨማሪ ዘላቂ መፍትሔዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት አለበት ሲል አሳስቧል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New