News

አዲስ ነገር – የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለኢትዮጵያ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የ 81 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
የህብረቱ ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል በቲውተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ እንደተዋያዩ ገልጸው በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ለዜጎች የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረው ምክክር ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ፤ ከሱዳንና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ግንኙነት ካላቸው ጎረቤት ሀገራት ጋር በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እንድታደርግ በውይይታቸው ያነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ህብረት አይነተኛ አጋር መሆኗንና ለቀጠናው መረጋጋት የምታበረክተው ሚናም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New