አዲስ ነገር – የእንደራሴዎቹ ውሎ
የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ ልዩ ጉባዔ፤ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ-ሀብታዊ እና ሌሎችም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡
የበጀት አመዳደብ ፍትሐዊነትን በተመለከተ፣ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ እንዲሁም የሰላም እና የፀጥታ ሁኔታዎችን በተመለከተ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን የስኳር ፕሮጀክቶች፣ የኮይሻ እና ጎረጎራ ፕሮጀክቶች፣ የመንገድ መሠረተ-ልማቶች የአፈጻጻም አሁናዊ ሁኔታቸው ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል፡፡
ከእንደራሴዎቹ ለቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የመንግስት ቀዳሚው ተግባር ሕግ እና ሥርዓትን ማስፈን ሲሆን፤ ሕዝብም በበኩሉ የመንግስትን ዕቅዶች፣ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች ተረድቶ መተግበር ከጀመረ፣ አብዛኛው ነገር አስቸጋሪ አይሆንም ብለዋል፡፡
በሌላ በኩልም የሽብር ተግባራት የሚወገዙ ሆነው ሳለ ሽብርን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚቻል እንዳልሆነ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዙሪያ መለስ ፈተና እና ኢትዮጵያ አሁን ለተጋረጠባት ጦርነት መፍትሔ የምናበጀው፤ የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማትን አጠናክረን በመገንባት ነው ብለዋል፡፡
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New