News

አዲስ ነገር – የቤት ኪራይ ጭማሪ

በአዲስ አበባ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስኪሻሻል ድረስ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እንደማይቻል ተገለጸ።
የከተማዋ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ትናንት በከተማዋ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ አስተዳደሩ በየ 3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰው በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ስላለ በቀጣይ በአስተዳደር ደረጃ የወጣው የቤት ኪራይ ደንብ እስኪሻሻል የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ሁኔታዎችን አይቶ ደንቡን እስኪያሻሽል ድረስ ምንም አይነት የቤት ኪራይ መጨመር እንደማይቻል ያስገነዘቡት ከንቲባዋ አከራዮችም ሆኑ ተከራዮች ይህን መገንዘብ እንዳለባቸውና ክልከላውን ተላልፈው የሚገኙ አከራዮች ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል።
ከንቲባ አዳነች በመግለጫቸው ዜጎች መብትና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩም አስገንዝበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ይሁንና ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከአንዳንድ ተከራዮች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ነዋሪዎች አሁንም ኪራይ ካልጨመራችሁ እየተባሉ ይገኛሉ።መብታቸውን ለማስከበር በሚሞክሩበትም ጊዜ ተነጋግራችሁ ፍቱት እየተባሉ እንደሆነ ነው የገለጹልን።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New