Sports

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በምስራቅ አፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ተጋጣሚዎቹ ታውቀዋል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በምስራቅ አፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ተጋጣሚዎቹ ታውቀዋል::

የ2014 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ኢትዮጵያን ወክሎ በምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት የክለቦች ሻምፒዮና ይሳተፋል፡፡ ቡድኑም በወርሃ ነሀሴ በሚደረገው ውድድር በምድብ 1 ከ ዛንዚባሩ #ዋሪየርስ እንዲሁም ከብሩንዲው #ፎፊላና እና ሩዋንዳው #ኤኤስ ኪጋሊ ተደልድሏል፡፡

ከነሃሴ 8 እስከ ነሃሴ 15 ድረስ በታንዛንያ አስተናጋጅነት በሚደረገው ውድድርም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን አባላት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከ ዛንዚባሩ ክለብ ዋሪየርስ ጋር ያደርጋሉ ፡፡ ንግድ ባንኮች ቀሪ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ደግሞ ከ ብሩንዲው ፎፊላ እና ከሩዋንዳው ኤኤስ ኪጋሊ ጋር በተከታታይ የሚያደርጉ ይሆናል ።

በ2022 ወርሃ ጥቅምት ሞሮኮ ለምታስተናገደው የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ለማለፍ በሚደረገው የምስራቅ አፍሪካ ክለቦች ማጣሪያም ንግድ ባንኮች ውድድራቸውን በበላይነት ካጠናቀቁ በ አፍሪካ የሴቶች የክለቦች ውድድር የሚሳተፉ ይሆናሉ፡፡
ሪፖርተር፡ ፈይሰል ዛኪር

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

አዲስ ነገር / What’s New

EBSTV WRLDWIDE

EBSTV WRLDWIDE

EBS