News

አዲስ ነገር – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነገው’ለት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም. በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔው በድምፅ መስጫ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አሠራጭቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል ።

ቦርዱ ለዝግጅት ክፍላችን ባደረሰው መረጃ መሠረት ሥርጭቱን ያከናወነው በ31 ማዕከላት ሥር ባሉ 3771 ምርጫ ጣቢያዎች ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ብርብርና ቁጫ ላይ የተከፈቱ የተፈናቃይ ጣቢያዎች ናቸው።

ሥርጭቱ የተከናወነው ከጥር 25 እስከ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን ፤ ምርጫ ጣቢያዎቹም በነገው ዕለት ለሚከናወነው የሕዝበ ውሣኔ የድምፅ መስጠት ሂደት በሙሉ ዝግጅት ላይ ይገኛሉም ብሏል ።

ጣቢያዎቹ በነገው ዕለት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ክፍት የሚሆኑ ሲሆን፤ ቦርዱ መራጮች በተጠቀሰው ሰዓት ወደተመዘገቡበት ጣቢያ በመሄድ ድምፃቸውን እንዲሰጡ አሳውቋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New