EthiopiaNews

ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ

የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ በነገው እለት ነሐሴ 1/2016 ዓ.ም ልዩ የውጪ ምንዛሪ ጨረታ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል። ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያወጣው ማስታወቂያ እንደሚያሳየው የውጭ ምንዛሪ የሚፈልጉ ባንኮች በነገው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሚቆየው በልዩ ጨረታው እንዲሳተፉ ጠይቋል።

እንደአስፈላጊነቱ የገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀጣይም ተመሳሳይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎች እንደሚካሄዱ ባንኩ አስታውቋል።