EthiopiaNews

ፍርድ ቤቶች ተዘጉ

የ2016 በጀት ዓመት መጠናቀቅን ተከትሎ ከዛሬ ነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ድረስ ፍርድ ቤቶች በከፊል ለእረፍት ዝግ እንደሚሆኑ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናግሯል።

ነገር ግን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ አስቸካይ የሆኑ በሰዎች መብት እና በሃገር ልማት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያስከትሉ የሚችሉ አስቸኳይነታቸው በችሎቱ የሚታመንባቸው መሰል ጉዳዮች በተረኛ ችሎት የዳኝነት አገልግሎቱ ስለመቀጠሉ አስረድቷል። ሰበር አጣሪ ችሎት በመደበኛ ጊዜ የሚሰርዋቸውን አጣርተው ውሳኔ የመስጠት ስራቸውን ከነሃሴ 1 ቀን እስከ 30 2016 አ.ም ድረስ በመደበኛነት የዳኝነት አገልግሎት መስጠት ይቀጥላሉ ተብልዋል፡፡