3 ቀናት ብቻ ቀሩት!
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ትተክልበታለች ተብሎ ቀን የተቆረጠለት ነሐሴ 17/ 2016 አርብ ዛሬን ጨምሮ 3 ቀናት ብቻ እንደቀሩት ጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቭዝን ማስታወስ ይወዳል።
በዚህ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አዋቂዎች ከ20 በላይ ፣ ታዳጊዎች ደግሞ ከ10 በላይ ችግኞችን በመትከል ለሀገር ያላቸውን ፍቅር እና ለትውልዱ ያላቸውን ስጦታ እንደሚገልጥበት የሚጠበቀው እለቱ የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል ነው።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃገሩን አረንጋዴ ሸማ የሚያለብስበት ታሪካዊ ቀን እንደሚሆን ይታመናል።