የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች !
በአማራ ክልል በዚህ አመት በ2016 ዓ.ም ብቻ ከ92 በላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መፈጸማቸዉን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታውቋል።
የክልሉ ፖሊስ የህፃን ሄቨን ጉዳይን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደገለጸው እዚህ አይነት ወንጀለኞችን ወደ ህግ ፊት ለማቅረብ ፖሊስ የሚቻለውን ቢያደርግም በህብረተሰቡ በኩል መረጃ በመስጠት በኩል ችግር እንዳለ ገልጾ ፤ በተለይ የቤት ውስጥ ጥቃቶች በቅርብ ሰውና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ አዳጋች በሆነ አግባብ የሚፈፀሙ በመሆናቸው ለፖሊስ የምርመራ ስራ አስቸጋሪ ነው ያለው ፖሊስ በክልሉ ተመሳሳይ ወንጀሎች እንደሚፈጸሙ ገልጿል።
ማህበረሰቡ የህፃን ሄቨንን ጉዳይ ትኩረት እንደሰጠው ሁሉ ነገ ለሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች መረጃና ማስረጃ በመሆን ፍትህን በጋራ እንድናረጋግጥ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።