በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ዙሪያ ሕገ-ወጥ ድርጊት የፈጸሙ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ 658 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት የፌዴራልና የክልል ተቋማትን ያካተተና የነዳጅ ስርጭቱን 24 ሰአታት የሚከታተል የሁኔታዎች ልዩ የመከታተያ ክፍል መቋቋሙን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ላይ ነው።
ሚኒስትሩ ጨምረውም ከ720 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ተይዞ ለመንግሥት ገቢ ሆኗል ብለዋል።
መረጃው ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
