EthiopiaNews

የማዳበሪያ ስርጭት

🔸የግብርና ሚኒስቴር ለ2018/19 የምርት ዘመን 16.3 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለስርጭት ዝግጁ መደረጉን አስታወቀ።

🔸ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በምርት ዘመኑ በበልግ እና መኸር በአጠቃላይ 25 ሚሊዮን ሄክታር ለማልማት ታቅዷል ብሏል።

🔸ለምርት ዘመኑ እስካሁን 20 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ የቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 16.3 ሚሊዮን ኩንታል ለስርጭት ዝግጁ ሆኗል።

🔸የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ቀሪ የማዳበሪያ ፍላጎታችንን ለማሟላት ግዢ በመፈፀም የማጓጓዝ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

🔸ሚኒስትሩ በዓለም የማዳበሪያ ዋጋ መጨመር የአርሶ አደሮችን የመግዛት አቅም እንዳይፈታተን መንግስት 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ብለዋል።

👉መረጃው ከግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ይፋዊ የማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews