EthiopiaNews

ከገበያ የታገዱ ምርቶች

🔸የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞችና በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች በሚገኙ 570 የንግድ ተቋማት ላይ ባደረገው ፍተሻ አስገዳጅ የጥራትና የገላጭ ጽሁፍ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሕገ-ወጥ ምርቶች በገበያ ላይ መገኘታቸውን ገልጿል።

🔸ባለስልጣኑ እነኚህ ምርቶች መስፈርቱን የማያሟሉ ፤ እኛ ያልመዘገብናቸው ፤ ጥራት እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ስለሆኑ እንዳትጠቀሙ ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

🔸ከአዲስ አበባ ውጭ በአዳማ ፣ቢሾፍቱ፣ዱከም፣ ሰበታ፣ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ለገጣፎና ገላን በተደረጉ ምርመራዎች 32 ዓይነት የገበታ ጨው፣19 ዓይነት የምግብ ዘይት፣6 አይነት የለውዝ ቅቤ እንዲሁም የማርና የከረሜላ ምርቶችን ማገዱን ገልጿል፡፡

🔸አክሎም ማናችውም ምርቶች በግልጽ የሚታይ ገላጭ ጽሁፍ ሊኖራቸው ፣የአምራች ድርጅት ስምና ሙሉ አድራሻ፣የምርቱ የወል ስም ፣ የምርቱ ክብደት፣ የተመረተበትና የሚያበቃበት በግልጽ ሊቀመጥ እንደሚገባ ተናግሯል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews