የትንሣኤ በዓል
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2018 ዓ/ም የትንሣኤ በዓል በሰላም መከበሩን አስታወቀ።
ፖሊስ ትናንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ካጋጠመ ድንገተኛ የሞት አደጋ ውጭ የተለየ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ በበዓሉ ዋዜማ ሆነ በበዓሉ እለት አላጋጠመም ሲል ገልጿል።
ሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጆኒ ጋራዥ አካባቢ ጠዋት ላይ የ59 ዓመት ግለሰብ በበሬ ተወግተው ህይወታቸው ማለፉን ፤ በሌላ ሰው ላይም ጉዳት መድረሱን ገልጿል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews