ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎች
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ 400 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ከተመላሾች መካከል ከ800 በላይ ወንዶች፣ ከ600 በላይ ሴቶችና 76 ጨቅላ ህፃናት የሚገኙበት ሲሆን ከ80 በላይ ያህሉ ደግሞ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።
መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ64 ሺህ 300 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለሳቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
