የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለኢትዮጵያ
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን የበጀት ድጋፍ ማስቀጠሉን አስታወቀ።
የህብረቱ የአለም አቀፍ ትብብር ኮሚሸነር ጆሴፍ ስኬላ ለኢትዮጵያ የ140 ሚሊዮን ዩሮ የበጀት ድጋፍ መመደቡን ተናግረዋል።
የበጀት ድጋፉ በኢትዮጵያ የኢነርጂ፣ የጤና እና የአይሲቲ ዘርፎችን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ህብረቱ ግሎባል ጌት ዌይ በተባለው መርሃ ግብሩ በኩል ለኢትዮጵያ የዲጅታል ዘርፍ 150 ሚሊዮን ዩሮ እና ለኤሌክትሪክ ኃይል ማስፋፊያ የሚውል 269 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
