የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድጋፍ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለግብርና እና ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የሚውል የ110 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ማግኘቱን አስታወቀ።
ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ከተገኘው ጠቅላላ ድጋፍ ውስጥ 50 በመቶው በሴቶች ለሚመሩ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እንዲውል ተመድቧል።
ከገንዘቡ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ማኅበረሰቡ የአካባቢ እና የኢኮኖሚ ድንገተኛ አደጋዎችን እንዲቋቋም ለሚያስችሉ የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ ስራዎች ይመደባል።
ይህ መርሃ-ግብር ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ቅድሚያ በመስጠት፣ የኢትዮጵያን የግብርና ምርት ሰንሰለት እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተገኘ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
