የአከርካሪ ቀዶ ህክምና ማዕከል
የጤና ሚኒስቴር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ግቢ የተገነባው የአከርካሪ ቀዶ ህክምና ማዕከል ተመርቆ ስራ መጀመሩን አስታወቀ።
የአከርካሪ ቀዶ ህክምና ማዕከሉ የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ በኢትዮጵያ የእስራኤል ም/አምባሳደር እንዲሁም በርካታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
ሚኒስቴሩ በአሜሪካውያን እስራኤላውያን የተቋቋመው በምህፃሩ ጄዲሲ የተባለው ተቋም ማእከሉ እንዲገባ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ሕይወት የሚቀይሩ ቀዶ ህክምናዎች ግለሰብ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰብና በማህበረሰብም የሚያመጣው ለውጥ ትልቅ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሚነስትሯ የጤና ሚኒስቴር የነርቭ እና የጀርባ አጥንት ቀዶ ህክምናና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት፣የማገገሚያ ስርአቶችን ለማጠናከር፣ እና እነዚህን አገልግሎቶች በአገር አቀፍ ደረጃ በቀጣይነት የሚያስቀጥል የባለሙያ ኃይል ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።
መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
