የአፍሪካ-አውሮፓ የጤና አጋርነት
የጤና ሚኒስቴር የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት ከ100 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የጤና አጋርነት ድጋፍ ይፋ ማድረጋቸውን አስታወቀ።
የአፍሪካን የጤና ደኅንነት፣ ጽናትና ሉዓላዊነት በማጠናከር ረገድ ትልቅ ምዕራፍ የሆነውን የአፍሪካ-አውሮፓ ህብረት የጤና አጋርነት የድጋፍ ፓኬጆች በሶስት አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጠንካራ ስርዓት፣ ጠንካራ ተቋማት እና ለማህበረሰቡ የተሻሉ የጤና ውጤቶች እንዲመጡ ከአፍሪካ ሲዲሲ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከሁሉም አጋሮች ጋር በቅርበት ለመስራት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነች ብለዋል።
መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
