የኢራን ተኩስ አቁም መራዘም
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገራቸውና በኢራን መካከል እየተደረገ ላለው ድርድር ጊዜ ለመስጠት የኢራንን የተኩስ አቁም ስምምነት ማራዘማቸውን ገለፁ።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኢራን ለድርድሩ መሳካት የሚጠቅም የተሟላ የሰላም ዕቅድ ይዛ እስክትቀርብ ድረስ በቴህራን ወደቦች ላይ የጣሉት እገዳ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰው የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬ የሚያበቃ የነበረ ቢሆንም ሁለቱ ሀገራት በፓኪስታን ዳግም ተገናኝተው ሳይደራደሩ አሜሪካ በተናጥል ተኩስ አቁሙን ማራዘሟ ነው የተሰማው፡፡
ሆኖም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለዚህ ውሳኔያቸው የፓኪስታን የማግባባት ስራ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን መጥቀሳቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
