EthiopiaNews

የኮሚሽኑ ውሳኔ

የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ በ46 የእርሻ ትራክተሮችና ተጓዳኝ ማሽነሪዎች ግዥ የጨረታ ሂደትን አቋረጠ፡፡

ኮሚሽኑ ይሄንን ውሳኔ የወሰነው ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሲጠረጥር ወይም ጥቆማ ሲደርሰው ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል ጥናት በማካሄድ ሂደቱ እንዲቋረጥ የማድረግ ስልጣኑን በመጠቀም መሆኑን ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ግዥ ግልፅ ጨረታ ሂደትን እንዲቋረጥ ማድረጉን የጠቀሰው ኮሚሽኑ የገበያ ዋጋ ጥናት አለማድረግ፣ የግዥ ጨረታው ከመውጣቱ በፊት ምስጢራዊ መረጃ መውጣቱ፣ የተቋሙ ባለሙያ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታውን ያልተወጣና የጨረታ ሂደቱ የጥቅም ግጭት የታየበት መሆኑ ለግዥ ሂደቱ መቋረጥ ምክንያት ከሆኑ ግኝቶች መካከል መሆናቸውንም ጠቁሟል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews