ኢትዮጵያን የሚያካትተው እርምጃ
ዓለም አቀፍ የቡና አምራችና ማቀነባበሪያ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን የሚያካትትና በቡና ገበያ ላይ የተደቀነውን ፈተና ለመቋቋም እንዲሁም የደን ጭፍጨፋን በሳተላይት ለመቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት ይፋ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
ይሀው ፕሮግራም ስምንት ግዙፍ የቡና ላኪና አምራች ድርጅቶች ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን በሳተላይት ምስልና በሰው ሰራሽ አስተውሎ በመታገዝ የቡና እርሻዎችን ከደኖች ለይቶ በትክክል ለመመዝገብ የሚያግዝ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ኩባንያዎቹ እርምጃውን ለመውሰድ የተገደዱት የአውሮፓ ሕብረት በደን ምንጠራ በተገኘ መሬት ላይ የለማ ቡና ወደ ገበያው እንዳይገባ የሚጥለውን ሕግ ተከትሎ ሲሆን እስካሁን ባለው የተዛባ የካርታ መረጃ ምክንያት በጥላ ስር የሚለማ የኢትዮጵያና የጎረቤት አገራት ቡና በስህተት እንደ ተፈጥሮ ደን ተቆጥሮ ከገበያ ሊታገድ ይችላል የሚል ስጋት ባለበት በዚህ ወቅት ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
