EthiopiaNews

የተዘጉት የምርጫ ጣቢያዎች

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ እንዲያከናውኑ ከተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 22ቱ ህገወጥ ድርጊት በመፈጸማቸው ምክንያት እንዲዘጉ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የተዘጉት የምርጫ ጣቢያዎች መስራት የሚጠበቅባቸውን ስራ ወደ ጎን በመተው ህግን ያላከበረ አሰራር በመከተላቸው መሆኑንም ቦርዱ በትላንትናው ዕለት የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ላይ ጠቅሷል፡፡

እንዲህ ዓይነት ድርጊት ላይ የተሳተፉ የምርጫ አስፈፃሚዎችም ላይ እርምጃ መውሰዱን ያስታወቀው ቦርዱ የተዘጉት የምርጫ ጣቢያዎችም በኦሮሚያ 12፣ በሶማሊ 6፣ በሲዳማ ክልል 2፣ በአማራ 1 እና ሐረሪ ክልል 1 መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባም ሃምሳ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበዋል ብሏል።
ከዚህ ውስጥ ከ45 ሚሊዮን በላይ በማንዋል 5 ሚሊዮን በላይ ደግሞ በዲጅታል በኩል እንደተመዘገቡ መሆናቸውንም አሳውቋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv