EthiopiaNews

ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዳጅ ሥርጭት ግብረ ኃይል በሕገወጥ የነዳጅ ዝውውር የተሳተፉ 256 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

ግብረ ኃይሉ አክሎም ባለፍው አንድ ወር ውስጥ ለከተማ አስተዳደሩ የተደለደለው የናፍጣ መጠን 38 ሚሊዮን ሊትር ገደማና ከዚህም ውስጥ 32 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነው ሊትር ለመደበኛ ነዳጅ ተጠቃሚዎ እንዲቀርብ መደረጉ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በፌደራል ደረጃ ተለይተው የተፈቀደላቸው ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ ለተፈቀደላቸው ኢንዱስትሪዎችና የከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ከአንድ ሺህ በላይ ተቋማት በአጠቃላይ 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ በትስስር እንዲወስዱ መደረጉንም ጠቁሟል።

በዚህ ሂደት በህገወጥ የነዳጅ ዝውውር የተሳተፉ 256 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለጸው ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል አመራሮች፣ የጸጥታ ኃይሎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የማደያ ሰራተኞች፤ ህገ ወጥ ሰልፍ አሰላፊ ወጣቶች፣ ደላላዎችና ሾፌሮች እንደሚገኙ አሳውቋል።

በቀጣይም የነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭትና የአገልግሎት አሰጣጡ ይበልጥ እንዲሻሻል ለማስቻል የስርጭትና ቁጥጥር ስርዓቱን ማጠናከር እንደሚገባ ከግብረ ኃይሉና ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር የመከሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዐባይ አሳስበዋል። መረጃው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv