የ9 ወራቱ የተመዘገቡ ኩነቶች
በ2018 በጀት አመት 9 ወራት ከ28 ሺህ 600 በላይ ጋብቻ ሲመዘገብ 4 ሺ 450 ደግሞ በወቅታዊና የዘገየ የፍቺ መመመዝገቡን የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው በ9 ወራት ውስጥ ከ324 ሺ 300 በላይ ልደት፣ 28 ሺ 600ጋብቻ፣ 19 ሺ 500 ግድም ሞትን ጨምሮ 382 ሺ 300 ኩነቶች መመዝገቡን ገልጿል።
በሌላ በኩል 142 ሺ 159 ያላገባ ማስረጃ አገልግሎት መስጠቱን ሲገልጽ ከ600 ሺ 500 በላይ ነዋሪዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመመዝገብ አገልግሎት መስጠት መቻሉም ተጠቁሟል።
ከተሰጠው የነዋሪነት መታወቂያ ውስጥ 99.78% በዲጂታልና 0.22 በመቶ ደግሞ በማንዋል መስጠቱን ኤጀንሲው አስታውቋል።
እንዲሁም ባለፈው 9 ወር ብቻ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተገልጋዮች ከማዕከል እስከ ወረዳ አገልግሎት ያገኙ መሆኑም ተገልጿል::
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
