የባለስልጣን መ/ቤቱ ጥሪ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የንግድ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሰጪዎች መረጃዎቻቸውን ለባለስልጣን መ/ቤቱ እንዲያቀርቡ ጥሪ አቀረበ።
መ/ቤቱ ይሄን ያለው ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ፈጣን፣ ግልጽ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የዲጂታላይዜሽን ሥራ በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
መ/ቤቱ ይህንን አዲስ የዲጂታል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባት የተሟላ የተቋማት መረጃ በሲስተሙ ውስጥ መካተት እንዳለበት ገልጿል።
መ/ቤቱ ሁሉም የንግድ ብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃዶች የሚጠበቅባቸውን መረጃዎች እስከ ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም ድረስ ማሟላት ብሏል።
መ/ቤቱ ከንግድ መገናኛ ብዙኃን ከሚፈልጋቸው ቁልፍ መረጃዎች ውስጥ የተቋሙ ስራ አሥኪያጅ፣ ኤዲተር፣ ባለቤት እና የፕሮግራም ኃላፊ ለውጥ ከተደረገ ማስረጃው፣የድርጅቱ የስራ ክንውን ሪፖርት፣ የጣቢያው የፋይናንስ ምንጭ ማስረጃ፣ እና ዓመታዊ የወጪ እና የገቢ ሪፖርት ናቸው።
መረጃው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
