EthiopiaNews

የጥላሁን ሃውልት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስድስት ኪሎ አካባቢ የተገነባውን የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠን መታሰቢያ ሐውልት መርቀዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣የጥበብ ቤተሰቦች፣አንጋፋና ወጣት አርቲስቶች እንዲሁም በርካታ አድናቂዎቹ ተገኝተዋል።

ይህ የመታሰቢያ ሐውልት አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የነበረውን ጉልህ ሚና እና ለበርካታ አስርት ዓመታት ያበረከተውን የማይረሳ አስተዋጽኦ የሚዘክር ነው።

አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉሥ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን፤ ከ400 በላይ የሚሆኑ ሥራዎቹ የሀገሪቱን ባህል፣ ፍቅር እና ማህበራዊ እሴቶች የጠበቁ ናቸው።

በስድስት ኪሎ የቆመው ሐውልት፣ አርቲስቱ ለጥበብና ለሀገሩ የከፈለውን መስዋዕትነት ለትውልድ የሚያስተላልፍ ከመሆኑም በላይ፣ ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሚሰጠውን ክብር የሚያሳይ ነውም ተብሏል።

ከከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች፤የሀገር ባለዉለታ የሆኑና በጥበብ ሞያቸዉ ለኢትዮጵያ ሀገራችን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በከተማችን አዲስ አበባ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋል በማለት የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ታዋቂ ሰዎች ሀውልት መገንባቱን አስታውቀዋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews