ፈረንሳይ በሆርሙዝ ሰርጥ
ፈረንሳይ የጦር ጄት ተሸካሚ መርከቦቿን ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ማንቀሳቀስ መጀመሯን አሳወቀች።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሀገራቸው የባህር ኃይል ከብሪታንያ የባህር ኃይል ጋር በመቀናጀት በሆርሙዝ ሰርጥ ለመፈጸም ለታቀደው ወታደራዊ ተልዕኮ ዝግጁ ለመሆን የጦር መርከቡ አሁን ላይ ቀይ ባህር መድረሱን ነው ያሳወቁት፡፡
በኒውክለር ኃይል የምትንቀሳቀሰው ቻርልስ ዴጎል የፈረንሳይ የጦር ጄቶች ተሸካሚ ግዙፍ መርከብ እስከ አጃቢዎቿ ከቀይ ባህር ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ታቀናለች ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም የፈረንሳይና ብሪታንያ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከአሜሪካ ይለያል ተብሏል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በሆርሙዝ ሰርጥ የባህር ትራንስፖርት ደህንነትን ማረጋገጥን አላማ ያደረገ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንደሚፈጽሙ የገለጹት ማክሮን ጉዳዩን በተመለከተም ከኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
