EthiopiaNews

ከትጥቅ ትግል የተመለሱ አካላት

ከትጥቅ ትግል የተመለሱ አካላት ምክክር የሀሳብ ልዩነቶችን መፍቻ ብቸኛ መንገድ መሆኑን እናምናለን ማለታቸውን ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ ቆይተው ከተመለሱ አካላት ጋር እያካሄደ በሚገኘው የውይይት መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ ከዚህ በፊት በተደረገ ውይይት በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና ሰላምን መርጠው የተመለሱ አካላት ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ 17 አጀንዳዎችን ሰንደው ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን አስታውሰዋል፡፡

እነዚህ ወገኖች ቀደም ሲል በተደረገው ውይይት ያነሳችኋቸውን ጥያቄዎች ኮሚሽኑ ለሚመለከተው አካል ማቅረቡን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ ይህ መድረክ ከኮሚሽኑ ጋር ይበልጥ ተቀራርባችሁ ለሰላም የምትሰረሩበት፣ የቀሩ ወገኖችን ወደ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ምክረሃሳብ የምትሰነዝሩበት ይሆናል ሲሉም ዓላማውን አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ በሌሎች አካባቢዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለማካተት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ውይይት 200 የሚደርሱ በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ የቆዩና አሁን ላይ ሰላምን መርጠው የተመለሱ ወገኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኮሚሽኑ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ ቆይተው ከተመለሱ የተወሰኑ አካላት ጋር የመጀመሪያ ውይይትና የአጀንዳ ርክክብ መድረክ ማካሄዱ አይዘነጋም፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv