የስርጭት መስመሮች ማስፋፊያ
የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ባከናወነው ስራ 9 ሺህ 588 ኪሎ ሜትር አዳዲስ የስርጭት መስመሮች ማስፋፊያ ወይም ዝርጋታ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 518 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 6 ሺህ 69 ኪ.ሜ ደግሞ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተከናወነ ሲሆን በተጨማሪም የኃይል አቅርቦቱን የሚያሳድጉ 3 ሺህ 683 የተለያዩ ዓቅም ያላቸው አዲስ የስርጭት ትራንስፎርመሮች ተከላ ተከናውኗል ብሏል፡፡
ነባሩ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አቅም ከማሻሻልና የኃይል መቆራረጥን ከመቀነስ አኳያ 62 ሺህ 274 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመካከለኛ መስመር እንዲሁም በ67 ሺህ 131 ትራንስፎርመሮች ላይ የቅድመ መከላከል ምርመራ መካሄዱንም ነው የገለጸው።
በዚህም ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑ ግኝቶች ውስጥ በስርጭት ኔትወርክ ላይ ከተገኙት 92 ከመቶ፤ በትራንስፎርመሮች ደግሞ 86 ከመቶ የሚሆኑትን የማስተካከያ እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል ብሏል።
የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችን በጥናት ከመለየትና እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ ያረጁ መስመሮችን መልሶ የመገንባት፣ ዓቅም የማሳደግና የማሻሻል እንዲሁም በዋናው ግሪድና በፀሃይ ኃይል አማራጭ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን በከፍተኛ ወጪ እየገነባ መሆኑንን ገልጿል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
