የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ መተግበሪያ
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ ሲስተም መተግበሪያ ወደስራ ሊገባ መሆኑን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው አዲሱ የአሽከርካሪዎች ብቃት መመዘኛ ሲስተም መተግበሪያ ላይ ያተኮረ ግምገማ ማድረጉን ባስታወቀበት መረጃው ላይ ነው፡፡
ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ተሳስሮ የተዘጋጀው ሲስተም አሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ምዝገባ የሚያካሂዱበት፣ የፈተና ቦታ እና ሰዓት እንዲያውቁ እንዲሁም ውጤታቸውን መልዕክት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ሚኒስቴሩ ተመዝጋቢዎች ፈተና ከመውሰዳቸው በፊት የሲስተሙን አጠቃቀም በተመለከተ ስልጠና እንደሚሰጣቸውም ገልጿል።
የተዘጋጀው ይህ ሲስተም አሽከርካሪዎችን መዝግቦ፣ አሰልጥኖ እና ፈትኖ በመጨረሻም የብቃት ማረጋገጫ COC እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን የተዘጋጀው መተግበሪያ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ በሲስተሙ አማካኝነት ምዝገባ እና ስልጠና እንደሚጀመርም ተናግረዋል።
መረጃው ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
