InternationalNews

የእሳተ ጎሞራ ፍንዳታ በኢንዶኔዢያ

በኢንዶኔዢያ የደረሰ የእሳተ ጎሞረ ፍንዳታ 3 ሰዎችን ሲገድል 20 ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው መጥፋቱ ተሰምቷል፡፡

በሀገሪቱ በሚገኘው ሀልማሄራ ደሴት ላይ የሚገኘው የዱካኖ ተራራ እሳተ ጎሞራ መፈንዳቱን ተከትሎ ተራራውን በመውጣት ላይ ከነበሩ ቱሪስቶች መካከል የሶስቱ አስክሬን ሲገኝ ደብዛቸው የጠፋው ሌሎቹን ቱሪስቶች የማፈላለግ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተነገሯል፡፡

የሀገሪቱ ፖሊስ የእሳተ ጎሞራው ፍንዳታ እስከ 10 ኪሎሜትር ብናኝ መረጨቱን የጠቀሰ ሲሆን በዚህ ብናኝ ውስጥ የተቀበሩ ቱሪስቶችን ነፍስ የማዳን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁሟል፡፡

ሳይንቲስቶች በአካባቢው የነበረውን የእሳተ ጎሞራ እንቅስቃሴ አጥንተው ከአንድ ወር በፊት ሰዎች ወደ አከባባው እንዳይቀርቡ እና በ4 ኪሎሜትር ከአካባቢው እንዲርቁ ማሳሰቢያ ሰጥተው እንደነበረ ጠቅሶ የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews