የተመለሱት ቅርሶች
በመቅደላ ጦርነት ወቅት በብሪታኒያ የተወሰዱ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ተመልሰዋል፡፡
ከ158 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ቅርሶቹ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል፣ የልብስ ቁራጮች እንዲሁም የወርቅ አምባር መሆናቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው በዚሁ ወቅት እንዳሉት ቅርሶቹ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲመለሱ የተደረገው የኢትዮጵያን የታሪክና የባህል አሻራዎች የማስመለስ ስራ አካል በመሆን ነው፡፡
ለረጅም ዘመናት በባዕድ ሀገር የቆዩት እነዚህ ቅርሶች ኢትዮጵያ የነበራትን ጥንታዊ ስልጣኔና ሉዓላዊነት የሚያሳዩ ትልልቅ የታሪክ ምስክሮች ናቸው የተባለ ሲሆን የቅርሶቹ መመለስ የኢትዮጵያን የታሪክ ባለቤትነትና የዲፕሎማሲ ስኬት የሚያሳይ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ እንደሚወሰድም ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ለቅርሶቹ ደማቅ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን ታሪካዊ የሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የወጡትን ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ስራ በስፋት እንደሚሰራም ተጠቁሟል።
በነገው ዕለት ግንቦት 7/2018 ዓ.ም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የቅርሶቹን ርክክብ እንደሚያደርግም ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
