EthiopiaNews

የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ

አሁን ያለው የዓለም አቀፍ ቀውስ በአስቸኳይ ካልተፈታ በሀገራት ድንበር የማይገታ አስከፊ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ አለመረጋጋት እንደሚያስከትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ለጥንካሬ፣ ለፈጠራ፣ ለትብብርና ለዘላቂነት መገንባት በሚል መሪ ሐሳብ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ነው።

ሚኒስትሩ ሁሉንም ሀገራት በፍትሃዊነት የሚያገለግል ዓለም አቀፍ ስርዓትን ለመገንባት የተቀናጀ የባለብዙ ወገን ጥረት በአስቸኳይ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን አሁን ያለው የዓለም አቀፍ ቀውስ በአስቸኳይ ካልተፈታ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ አለመረጋጋት እንደሚያስከትልም አስገንዝበዋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews