EthiopiaNews

የቅዱስ ሲኖዶሱ ማሳሰቢያ

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሁሉም ወገን ለኢትዮጵውያን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲፈጸም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳሰበ፡፡

በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው እለት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ የሰጠው ቅዱስ ሲኖዶስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉንም ጠቅሷል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የአርሲ ሀገረ ስብከትና የምእመናኑ የሰላም ጉዳይ የተመለከተ ሲሆን በአከባቢው በምዕመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ከመንግስት ጋር በመነጋገር እንዲፈቱ፣ ሕዝቡን እንዲያጽናኑ፣ ሀገረ ስብከቱንም በሊቀ ጵጵስና በቋሚነት እንዲመሩ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በቅዱስ ሲኖዶሱ መመደባቸውን አስታውቋል።

በተጨማሪም በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ ምሕረትና ፍትሕ እንዲያገኙ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉም ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews