የፑቲን የቻይና ጉብኝት
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገራቸውና የቻይና ግንኙነት መጠናከር ዓለምን የሚያረጋጋ ፍፁም ኃይል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ለሁለት ቀናት ጉብኝት ወደ ቻይና ከማቅናታቸው በፊት ሲሆን ሞስኮና ቤጂንግ ያላቸው ግንኙነት ለጋራ ሰላምና ዓለምአቀፍ እድገት እንጂ በሆነ ሀገር ላይ ባላንጣ ለመሆን ያለመ አለመሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
ፑቲን ሀገራቸውና ቻይና በዚህ መርህ መሰረት ዓለምአቀፍ ሕግን ለመጠበቅና የተመድን መርህ ለማስከበር እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡
ፑቲን በቤጂንግ የሁለት ቀናት ጉብኝት የሚያደርጉት ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙትን የመልካም ጉርብትናና ወዳጅነት ትብብር ስምምነት 25ኛ ዓመት በዓል ለማክበር መሆኑ ሲነገር ፑቲን ቤጂንግን የሚጎበኙት ደግሞ ትራምፕ መሰል ጉብኝት ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው፡፡ ዘገባው የአልጄዚራ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
