EthiopiaNews

የቪዛ ገደብ መነሳት

🔸የአውሮፓ ህብረት ወደ ሕብረቱ በሚገቡ ኢትዮጵያውያን ተጓዦች ላይ ጥሎት የነበረውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስታወቀ።

🔸ህብረቱ የቪዛ ገደቡን ያነሳው ኢትዮጵያ ዜጎችን በመመለስ እና በቪዛ አሰራሮች ላይ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ እንድታጠናክር ለማበረታታት ነው ተብሏል።

🔸ኅብረቱ ባደረገው ግምገማ በሕገወጥ መንገድ በህብረቱ አባል ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጐች የመለየት ፣ የአደጋ ጊዜ የጎዞ ሰነዶችን የማውጣት እና የመመለስ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ በኩል ያለው ትብብር በእጅጉ መሻሻል አሳይቷል።

🔸የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2024 ወደ ሕብረቱ በሚገቡ ኢትዮጵያውያን መንገደኞች ላይ የቪዛ ገደብ መጣሉ ይታወሳል።

🔸ሕብረቱ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያውያን መንገደኞች ላይ በጣለው የቪዛ ገደብ ሳቢያ መደበኛው የቪዛ ማመልከቻ ጊዜ ከ15 ቀናት ወደ 45 ቀናት ከፍ እንዲል እና ከአንድ በላይ መግባት የሚያስችሉ የቪዛ ፈቃዶችን የመስጠት አሰራር መታገዱ ይታወሳል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews