EthiopiaNews

የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚዎች ቁጥር

🔸በኢትዮጵያ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 43 ሚሊዮን መድረሱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

🔸ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 20 ሚሊየን ዜጎች ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲመዘገቡ ዲጂታል መታወቂያን ከ100 በላይ በሚሆኑ የመንግሥትና የግል ተቋማት አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር ዜጎች መረጃን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ማስቻሉን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ በትላንትናው ዕለት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።

🔸በሌላ በኩል በዲጂታል ኢኮኖሚ ወሳኝ የሆነውን የሞባይልና የኢንተርኔት ተጠቀሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ በተሰራው ሥራ በሀገሪቱ በአጠቃላይ 97 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ተጠቃሚ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 84 ሚሊዮኑ በኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም 13 ሚሊየኑ ደግሞ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኩል የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews