እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ የባንክ ሂሳቦች
እንዳይንቀሳቀሱ የተደረጉ የባንክ ሒሳቦችና በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንኩ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የባንክ ሒሳብ ቁጥርን ከብሄራዊ መታወቅያ ፋይዳ ጋር የማስተሳሰር ሂደቱን በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም በበይነ መረብ እንዲያካሄዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በሀገሪቱ በተመረጡ ከተሞች ላይ የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከፋይዳ መታወቂያ ጋር እንዲተሣሠር የተቀመጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በትዕዛዙ መሠረት ደንበኞች እነዚህን ሒሳቦች ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገልጿል።
ይህንን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ የማስተሣሠር ጥያቄ ወደ ባንኩ እየቀረበለት መሆኑን በመጥቀስ ይህንን ጫና በመቋቋም ከደንበኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ አሠራሮችን ተግባራዊ እንዳደረገም ጠቅሷል።
ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 12 በተለየ ምክንያት እንዳይንቀሳቀሱ ከተደረጉት ሒሳቦች ውጪ የተሣሠሩ ሒሳቦችን ደንበኞች ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ሲደረግ ከግንቦት 12 ጀምሮ ደንበኞች ሒሳባቸውን እንዳስተሣሠሩ የመረጃ ሥርዓቱ በራሱ ጊዜ ገደቡን እንዲያነሣ መደረጉን ባንክ አስታውቋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
