የ6ኛ ክፍል እና የ8ኛ ክፍል ፈተናዎች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና የሚሰጥበት ጊዜን ይፋ አደረገ።
በዚህ መሰረት የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 8 ፣ 9 እና 10/2018 ዓ.ም እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ቢሮ ገልጿል።
በ6ኛ ከፍል 84,882 ተማሪዎች 199 የመፈተኛ ጣቢያዎች እንዲሁም በ8ኛ ከፍል 86,808 ተማሪዎች 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናዉን ለመውሰድ ተመዝግበዋል ተብሏል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
